ሕግ

ከኤች አይ ቪ ጋር ለሚኖሩ ሕሙማን አንዳንድ መብቶች እና ግዴታዎች አላቸው ፡፡ በኢንፌክሽን ቁጥጥር ሕግ ደንቡ መሠረት በኖርዌይ ውስጥ ለኤች አይ ቪ ሕሙማን ሕክምናዎች በነፃ ሲኖን እንደዚሁም ከሚከፈልም የግል ክፍያም ነጻ ነው ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ለጥርስ ሕክምና የአንዳንድ ወጪዎች ተመላሽ ገንዘብም ማግኘት ይችላሉ ፡፡

scheduleOppdatert: 16.12.2022

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ከኤች አይ ቪ ጋር ስለመኖርዎ መረጃ የመስጠት ግዴታ የለብዎትም ፡፡ ሁንም ለሐኪምዎ ግልጽ እንዲሆኑ እንመክራለን ፡፡ ሐኪሙ ጤንነትዎን በጥሩ ሁኔታ መከታተል እንዲችል እና እንዲሁም የሚሰጥዎ ሌላ ህክምና በኤች አይ ቪ መድኃኒቶች ላይ ተጽዕኖ የማያሳድር መሆኑን ለማረጋገጥ ሐኪሙ የታካሚውን የኤች አይ ቪ ምርመራ ማወቁ አስፈላጊ ነው ፡፡

የወንጀል መቅጫ ሕግ አንቅጽ 237 በሰዎች መካከል ከባድ ተላላፊ በሽታዎችን በሰዋች መካከል ስለማስተላለፍ ይገልጻል ፡፡ ስለ ተላላፊ በሽታ ማስተላለፍ እና አንድን ሰው ለበሽታው መተላለፍ በማጋለጥ ላይ ያተኮረ ነው ። ነገር ግን ተላላፊ በሽታው ሊተላለፍ የሚችልበት በቂ እና ግልጽ አደጋ ባለበት ወቅቶች ላይ ብቻ ነው ፡፡ አንድን ሰው ለኤ ች አይ ቪ ተላላፊ በሽታ ማጋለጡ በዚህ አንቀጽ ስር ሊያስቀጣው ይችላል ። ሆኖም ግን ብዙ ልዩ ከዚህ አንቀጽ ውጭ የሆኑ ሁኔታዎች አሉ ፡፡

  • ሕመተኛው ስኬታማ ህክምና ላይ ከሆነ ለሌሎች በበሽታው የማስተላለፍ አደጋ የለውም ፡፡ በጾታዊ ግንኙነት ወቅቶች በሽታው እንዳይተላለፍ ለመከላከል የሚቻለውን ሁሉ ካደረጉ ከቅጣት ነፃ ይሆናሉ ፡፡ ይህ ማለትም በኤች አይ ቪ ሕሙማን በሕክምና ላይ ያሉ ወይም ኮንዶም የሚጠቀሙ ሰዎች ሊቀጡ አይችሉም ማለት ነው፡፡
  •  ሕመምተኛው የወሲብ አጋሩ በሽታው እንዳለበትና ማስተላልፍ እንደሚችል አውቆ ወይንም ለተላላፊ በሽታ መጋለጡን  ፈቅዶ ከሆነ ህመምተናው አይቀጣም ። ይህ ማለት ደግሞ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ማለት አይደለም ነገር ግን የወሲብ አጋሩ የሁኔትው መግለጫን አግኝቶ  ግን “ራሱን ለተላላፊው በሽታው የተጋላጭነት አደጋ ላይ ከዳረገ ” ሕመምተኛው በሽታን በአስተላላፊነት ሊቀጣ አይችልም ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ህክምና ላይ ካልሆነ እና ተላላፊው በሽትውን ከምስተላለፍ ለመከላከል ሌሎች አስፈላጊ እና በቂ እርምጃዎችን የማይወስድ ከሆነ በሕግ ሊቀጣ  ይችላል ። በዚህ ሁኔት ተላላፊው በሽታ ተላለፎ ወይም ሳይተላለፍ ቢሆንም እንኳን ያስቀጣል። ለወሲብ ጓደኛው ካላሳወቀ ግለሰቡ በሕግ ሊቀጣ ይችላል።
  •  የሴትኛ አዳሪዎች እና በመርፌ አደንዛዥ እፆችን የሚወሰዱ እንዲሁም ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፍ በሽታን ከአስተላላፉ ከቅጣት ሁሉም ነፃ ናቸው  ፡፡

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።