camera_altFoto: Shutterstock

ኤች.አይ.ቪ ፣ መብቶች ፣ ኮቪ -19 እና ሂቭ ኖረር

ኤችአየቪ ኖርዌ (HivNorge)

ኤችአቪ ኖርዌ ከኤችአቪ ጋር ለሚኖሩ እና ኑሮአቸውን ኤች አይ ቪ የሚነካ ግለሰቦችን በኖርዌ ውስጥ የሚገኝ ብቸኛ የሆነ የሕሙማን ድርጅት ነው ።እንደዚሁም በተጨማሪም  በኤች አይ ቪ ተጠቂ  ግለሰቦች ፣ እንዲሁም የፕራይፕ ተጠቃሚዎችን እና በኤች አይ ቪ የምመበከል እድላቸውን ከፍተኛ ለሆኑ ሰዎች ጨምሮም ላላችው ማንኛውም ለፍላጎታችውም ተቋርቋሪ የፖለቲካ ድርጅትም ነው ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

ኤችአይ ቪ ምንድን ነው?

ኤች አይ ቪ በሽታን የሚከላከልን (immunforsvaret) የሰውነት ስርዓትን የሚያጠቃ ቫይረስ ነው ፡፡ ቫይረሱ ወደ ሰውነት ሲገባ የሰውነት የበሽታ መከላከያውን ቀስ በቀስ ያዳክማል ወይም ያጠቃል ይህንንም ጥቃት የሚቋቋም መድሃኒት ካልወሰዱ ሰውነትን ለበሽታ እና ለበሽታ መበከል ጥቃት ተጋላጭ ያደርጋል።

ተጨማሪ መረጃ

የኢንፌክሽን መንገዶች እና እራስዎን እንዴት መጠበቅ ይችላሉ

በኤች አይ ቪ ጋር የሚሆሩ ግለሰቦች ወይም ሕሙማን እና እንደዚሁም ስኬታማ ህክምና ላይ የሚገኙ እና በደማቸው ውስጥ ተለኪያዊ የቫይረስ ቁጥር መጠን የሌላቸውን ግለሰቦች በኤች አይ ቪ ለሌሎች ማስተላለፍ አይችሉም ፡፡ ኤች አይ ቪ እንዲሁ በማኅበራዊ ግንኙነት ማለተም በመሳሳም ፣ በመተቃቀፍ ፣ አንድን ኩባያ በመጋራት ወዘተ ተላላፊ በሽታ አይደለም ፡፡

ኤች አይ ቪ በዋነኝነት የሚተላለፈው ኤች አይ ቪ ካለበት እና ህክምና ላይ ከማይገኝ ሰው ጥንቃቄ የጎደለው ወሲባዊ ግኑኝነትን በመፈጸም ፣ ደም ከሌላ ሰው በማግኘት እና ከእናት ወደ ልጅዋ በእርግዝናዋ ፣ በመወለድ እና ጡት በምታጠባት ወቅቶች ሊተላለፍ ይችላል ፡፡
ራስዎን ከኤች አይ ቪ ለመከላከል የሚያበቁ ብዙ ዘዴዎች አሉ

ስኬታማ ህክምና ፣ ኤች አይ ቪ ካለባቸው እና በተሳካ በቂ ህክምና ላይ ካሉ ሰዎች በኤች አይ ቪ የመበከል አደጋ የለውም ፡፡ ይህ ማለትም ግለሰቡ ህክምናውን ይከተላል ፣ መድሃኒቱን ይወስዳል እናም ስለሆነም የቫይረሱ ቁጥር እጅግ በጣም አነስተኛ በሆነ መንገዱ ሲጠበቅ ለማንም ማለትም ጥበቃ በሌለው ሁኔታ በፆታዊ ግንኙነትም ሆነ በእርግዝና ወይም በወሊድ ወቅቶች ሊተላለፍ የማችል ነው ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

ለኤች አይ ቪ ምርመራ ማድረግ

በኤች አይ ቪ መበከልን  ለማወቅ የሚቻልበት መንገድ የኤች.አይ.ቪ ምርመራ በማድረግ ብቻ ነው ፡፡ ይህ ምርመራ መደበኛ ሀኪም ተመላላሽ ክሊኒክ ፣ አንዳንድ ድርጅቶች ውስጥ፣ ለወሲብ ጤና ጥንቃቄ እርዳታ የሚሰጥበት ተመላላሽ ሆስፒታል ማለትም     እንደ  ኦላፊያ ተመላላሽ ሆስፒታል (Olafiaklinikken) እና ወሲብ እና ማህበረሰብ (Sex og samfunn)(ከ25 ዓመት በታች ለሆኑ ብቻ ነው) ። ለኤች አይ ቪ ለመበከል ከፍተኛ ለሆነ አደጋ ተጋላጭነት ሁኔታ ሲያጋጥመው አንድ ግለሰብ  የኤች አይ ቪ ምርመራን መውሰድ በነፃ ያለምንም ክፍያ ይሆናል  ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

ምርመራው ውጤቱ  አዎንታዊ ወይም ፖዘቲፍ ከሆነ

ለኤች አይ ቪ ምርመራው ውጤት አዎንታዊ ወይም ፖዘቲፍ ከሆን ወደ ተላላፊ በሽታ የጤና ተቋም ተልከው ይሕክምና እግልግሎት እንዲያገኙ እድል ይቀርብሎታል ፡፡ ከኖርዌይ ውስጥ ከኤች አይ ቪ በሽታ ጋር ለተያዙ ህክምናዎች በሙሉ በነፃ ይሰጣሉ ፡፡

ኤች አይ ቪ በአሁኑ ዘመን ሥር የሰደደ ዘላቂ የሆነ የህመም ሁኔታ ሲሆን እንደማንኛውም ሰው ግን ረጅም ዕድሜ ዘመን መኖር ይቻላል ፡፡ ሆኖም ግን ለዚህ ረጅም እድሜ ለመብቃት የኤችአይቪ ሕክምናውን ወዲያውኑ መጀመር እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡ ይህ ለራሱ ጥቅም ብቻ ሳይሆን በአንጻራዊ ሁኔታው ሲታይ ከአጭር የህክምና እርዳታ በሁላ ግለስቡ በሽታውን ወደ ሌላ ግለሰብ ከማስተላለፍም ነጻ ይሆናል ማለትም ጭምር ነው።  የሕክምና ክትትሉ የሚከናወነው በተላላፊ በሽታ ክፍል  በሆስፒታል ውስጥ ነው ፡፡ ሕክምናው አንዴ ከተጀመረና እንደሚሠራ ወይም ስኬታም ውጤን መስጠቱን  ከተረጋገጠ በኋላ በዓመት ለአንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ የጥንቃቄ  ምርመራውን ማድረግ በቻ በቂ ይሆናል ፡፡ የኤች አይ ቪ ሕክምና ዛሬ በጣም ጥቂት የተጎዳኝ  ጉዳቶች ሲኖሩት አብዛኝውም ጊዜም በቀን አንድ ክኒን ብቻ ነው መውሰድም የሚያስፈልገው ።

ተጨማሪ መረጃ

ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

ተጨማሪ መረጃ

የአእምሮ እና ማህበራዊ ድጋፍ

በኤች አይ ቪ ተበካይ ሕሙማን አብሮ ከበሽታው ጋር ለመኖር ከባድ  ሁኒታዋች ሊያጋጥማቸው ይችላል ። ምክንያቱም በኅብረተሰቡ ውስጥ ብዙ ጭፍን ጥላቻዎች መኖርና እና እንደዚሁም ስለ ኤች አይ ቪ ያለው ዕውቀት አነስተኛ በመሆኑ ምክነያት  ነው ፡፡ ስለሆነም ድጋፍ ሊሰጥዎት የሚችል ሰው መኖራቸው እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡

ይህም ጓደኛ ፣ ቤተሰብ ፣ ሌሎች በኤች አይ ቪ የተበከሉ ሕሙማን  ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ደግሞ ለምሳሌ  ስብሰባዎች ላይ መገኘት  ወይንም ኤች አይ ቪ ኖርዌ (HivNorge) ድርጅ መሄድ ይችላሉ ፡፡ በኢንፌክሽን በሽታ ህክምና ክፍሎች ውስጥ ያሉ ሀኪሞች እና ነርሶች ጥሩ ድጋፍ ናቸው ሆኖም ግን ከኤች አይ ቪ ጋር አብረው ከሚኖሩ ግለሰቦችን ጋር መገናኘት በእውነቱ በኤች አይ ቪ የተያዘ ህይወት እንዴት እንደሚመስል የበለጠ ግንዛቤ እና እውቀት ለማኘት ያስችላል ፡፡ የሂቪ ኖርዌ የአቻ አገልግሎት (HivNorges likepersontilbud) ለኤች አይ ቪ ሕሙማን እና ለዘመዶቻቸው ከሌሎች የኤች አይቪ ሕሙማና ቤተሰቦቻቸው ተገናኝተው ልምድንና ምክርን ለመቀያያር የሚያስችል እድሎችን የሚቀርብ ድርጅት ነው ።

ተጨማሪ መረጃ

ሕግ

ከኤች አይ ቪ ጋር ለሚኖሩ ሕሙማን  አንዳንድ መብቶች እና ግዴታዎች አላቸው ፡፡ በኢንፌክሽን ቁጥጥር ሕግ ደንቡ መሠረት  በኖርዌይ ውስጥ ለኤች አይ ቪ ሕሙማን  ሕክምናዎች በነፃ ሲኖን እንደዚሁም ከሚከፈልም የግል ክፍያም ነጻ ነው ፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ለጥርስ ሕክምና የአንዳንድ ወጪዎች ተመላሽ ገንዘብም ማግኘት ይችላሉ ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

 መድሕን ወይም ዋስትና

መድሕን በሚገቡበት ጊዜ የጤና መረጃ እንዲያቀርቡ የሚጠይቁ አንዳንድ የመድሕን ዓይነቶች አሉ ፡፡ ከነዚህም መካከል የሕይወት እና የአካል ጉዳት መድሕኖ ናቸው ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

ሌሎች ዋስትናዎች ወይም መድህኖች

ኤች አይ ቪ ለሌሎች ኢንሹራንሶች ሊያመጥ የሚችለው ችግሮችን በሚመለከት ሁኔትው እንዲገለጽ የሚጠየቀው ዋስትናው በጤና ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ላላቸው ኢንሹራንሶች ወይም ዋስትናዎች ብቻ ነው። ለእንደዚህ አይነት ዋስትናዎች የጤና የምስክር ወረቀቶችን መጠየቅ  ይፈቀዳል፡፡ ይኸውም ለየሞት አደጋ መድሕን ፣ የአካል ጉዳት አደጋ መድሕን ፣ የሕክምና መድሕን ፣ የጤና መድህን ፣ በሕመም መቅረት የሚጋለግል መድሕን እና የአደገኛ የሕመም አደጋ መድህን ናቸው ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

የጉዞ መድህን

ወደ የጉዞ ዋስትና እና ስለ ኤች አይ ቪ መድሕን በሚመጣበት ጊዜ አግባብ ያለው ጠንቅ ያለ አስተሳሰብን መያዙ ጠቃሚ ነው ፡፡ በደንብ የሕክምና ክትትል የሚሰጠው የኤችአይቪ ኢንፌክሽን ሕመምተኛ ከሆኑና እና በኖርዌይ ውስጥ የሕክምና ክትትልን የሚያገኙ  ከሆነ እና በጉዞው ወቅቶች የተረጋጋ ሁኔት ላይ ከአሉ  በኤች አይ ቪ በሽታ ድንገተኛ ወይም ያልተጠበቀ ለውጥ ከተከሰተ የመድሕን ክፍያን ወጭዎችን መሸፍንን ያገኛሉ ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

ኤች አይ ቪ ኖርዌ (HivNorge)

ከኤች አይ ቪ ሕመም ጋር ቀጥታ ግኑኝነት በአለው ነግሮች ላይ ሕጋዊ ጥያቄ ከአሎት ወይም የሕግ አገልግሎት ማግኘት ከአስፈለግዎች ኤች አይ ቪ ኖርዊ ሊረዳዎች ይችላል ። በተጨማሪም የአጠቃል ምክር የመስጥትን አገልግሎትን ስለምናቀርብ ከኤች አይ ቪ የተያያዙ ሌሎች ጥያቄዎች ካሉዎት በምክር ልንረዳዎች እንችላለን፡፡

 ኤች አይ ቪ ኖርዌ  ከኤችአይቪ ጋር ለሚኖሩ ሕሙማን ወይም በኤች አይ ቪ ጋር በምንኛውም መንገድ የተያያዥነት ያላችው ሰዎች ሁሉ እንደዚሁም ፒአር ኢፒ (PrEP) ተጠቃሚያትን ጨምሮ ሕክምናዊ  አገልግሎት የማይሰጥ የውይይት አገልግሎት አቅርቦት አለን ፡፡ ከኬሚሜፍሪንድሊ (Chemfriendly)ድርጅት ጋር በመተባበር ለኬሚክስ ወሲብ ተጠቃሚዎች (chemsexbrukere) እና ለሌሎች አደንዛዥ እጽ ለሚጠቀሙ ለግብረ ሶደማውያን የውይይት አቅርቦት አገልግሎትም እንሰጣለን ። የአስተርጓሚ ሚያስፈልግ ከሆነ አብረን በአንድ ላይ ከገመገምን በሆላ እንዳአስፈላጊነቱ ይቀርባል ፡፡

ተጨማሪ መረጃ

ድጋፍየትማግኘትይችላል

በአጠቃላይ  በኖርዌይ ውስጥ በኤች አይ ቪ ለተያዙ ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጡ በርካታ ድርጅቶች አሉ ፡፡ ከዚህ በታች  የተወሰኑት እርዳታ የሚሰጡ ድርጅቶች ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ  በተጠቀሱት ድርጅቶች በሙሉ ልዩ ባለሙያዎችን በማግኘት ወይም ከሌሎች ኤች አይ ቪ ጋር ከሚኖሩ ገለሰቦች  ጋር ለመገናኘት እድል ያገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃ

ኤች አይ ቪ እና ስል ኮቪድ- 19 (Hiv og Covid-19)

ከኤች አይ ቪ ሕሙማን በመሆን በሚኖሩበት ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የመጠቃት ወይም በኳቪድ -19 መበከል ከባድ የህመም  አደጋ የተጋለጡ አይደሉም ፡፡ ዝቅተኛ የሆነ የበሽታ የመከላከል አቅም ካለዎት (ማለትም ከ 200 ሲዲ 4 ቆጠራዎች በታች ወይም     (dvs. under 200 CD4-tall)) እና ሌሎች ተጨማሪ ከባድ በሽታዎች  ከአለበዎት ግን ልመጠቃት ከፍተኛ የሆነ ተጋላጭነት ሊኖርዎት ይችላል ፡፡

የኤች አይ ቪ ኖርዌ (HivNorge) በተለያተለያዩ ቋንቋዎች ስለ ኤች አይ ቪ እና ስል ክኳቪድ- 19 (hiv og covid-19 på flere språk )መግለጫዎችን አውጥተዋል ።

ተጨማሪ መረጃ

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።