ኤችአይ ቪ ምንድን ነው?

ኤች አይ ቪ በሽታን የሚከላከልን (immunforsvaret) የሰውነት ስርዓትን የሚያጠቃ ቫይረስ ነው ፡፡ ቫይረሱ ወደ ሰውነት ሲገባ የሰውነት የበሽታ መከላከያውን ቀስ በቀስ ያዳክማል ወይም ያጠቃል ይህንንም ጥቃት የሚቋቋም መድሃኒት ካልወሰዱ ሰውነትን ለበሽታ እና ለበሽታ መበከል ጥቃት ተጋላጭ ያደርጋል።

scheduleOppdatert: 22.07.2021

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ኤድስ (AIDS)(የበሽታ መከላከያ የሰውነት ክፍል ድክመት ሲንድሮም / acquired immunodeficiencysyndrome) በኤች አይቪ የበሽታ መበከል  ምክንያት በተዳከመ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅማቸው መድከም  የተነሳ የሚከሰቱ ተመሳሳይ የሆኑ በርካታ በሽታዎችን የሚያጠቃልል የጋራ  የመተጠሪያ ቃል ነው ፡፡ በኖርዌይ ውስጥ በጥቂቱ ስራ ላይ የዋለ የሕመም መጠሪያ ነው። ለኤች አይ ቪ መበከል ሕክምና ሲጀምሩ በሽታ የመከላከል የሰውነት ስርዓትዎ ይጨምራል እናም ከዚህ በኋላ የኤድስን የበሽታ ያለበት ግለሰብን መስፈርታት  አያሟሉም ማለት ነው፡፡ 

ከኤች አይ ቪ የሚያድን ወይም የሚፈውስ ህክምና የለም ። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት የሚሰጠው ውጤታማ ህክምና ለከባድ በሽታ ችግሮች ተጋላጭነትን የሚቀንስ ከመሆኑም በላይ እንደዚሁም ሌሎችን የመበከል አደጋውንም ያስወግዳል ፡፡ 

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።