የአእምሮ እና ማህበራዊ ድጋፍ

በኤች አይ ቪ ተበካይ ሕሙማን አብሮ ከበሽታው ጋር ለመኖር ከባድ ሁኒታዋች ሊያጋጥማቸው ይችላል ። ምክንያቱም በኅብረተሰቡ ውስጥ ብዙ ጭፍን ጥላቻዎች መኖርና እና እንደዚሁም ስለ ኤች አይ ቪ ያለው ዕውቀት አነስተኛ በመሆኑ ምክነያት ነው ፡፡ ስለሆነም ድጋፍ ሊሰጥዎት የሚችል ሰው መኖራቸው እጅግ አስፈላጊ ነው ፡፡

scheduleOppdatert: 22.07.2021

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ይህም ጓደኛ ፣ ቤተሰብ ፣ ሌሎች በኤች አይ ቪ የተበከሉ ሕሙማን  ሊሆኑ ይችላሉ ወይም ደግሞ ለምሳሌ  ስብሰባዎች ላይ መገኘት  ወይንም ኤች አይ ቪ ኖርዌ (HivNorge) ድርጅ መሄድ ይችላሉ ፡፡ በኢንፌክሽን በሽታ ህክምና ክፍሎች ውስጥ ያሉ ሀኪሞች እና ነርሶች ጥሩ ድጋፍ ናቸው ሆኖም ግን ከኤች አይ ቪ ጋር አብረው ከሚኖሩ ግለሰቦችን ጋር መገናኘት በእውነቱ በኤች አይ ቪ የተያዘ ህይወት እንዴት እንደሚመስል የበለጠ ግንዛቤ እና እውቀት ለማኘት ያስችላል ፡፡ የሂቪ ኖርዌ የአቻ አገልግሎት (HivNorges likepersontilbud) ለኤች አይ ቪ ሕሙማን እና ለዘመዶቻቸው ከሌሎች የኤች አይቪ ሕሙማና ቤተሰቦቻቸው ተገናኝተው ልምድንና ምክርን ለመቀያያር የሚያስችል እድሎችን የሚቀርብ ድርጅት ነው ።

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።