camera_altFOTO: Hakan Nural/Unsplash
ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።
በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።
scheduleOppdatert: 31.12.2021
createForfatter: Sekretariatet
labelEmner: hiv og covid-19Trygg covid-19-vaksine
በዩኤንኤድስ UNAIDS መሰረት የኮቪድ-19 ክትባቶች ኤች አይ ቪ የተያዙ ሰዎችን ጨምሮ ለአብዛኛዎቹ ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።
PDF: ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።
ክትባቶቹ ኮቪድ-19ን የሚያመጣው ቫይረስ የሆነውን ከ SARS-CoV-2 የሚመጡ አንዳንድ ጀነቲካዊ ቁሶችን ይይዛሉ። ይህም የራሳችንን በሽታ የመከላከል አቅም ከቫይረሱ የሚከላከሉ ፀረ እንግዳ አካላትን እንዲያመነጭ ያነሳሳል። በእድገት ላይ ያሉ ወይም በአሁኑ ጊዜ ተቀባይነት ካገኙ ክትባቶች ውስጥ የትኛውም ክትባቶች ህይወታዊ ቫይረሶችን አይጠቀሙም፡ እና ስለዚህ ደካማ የበሽታ መቋቋም አቅም ላላቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆን አለበት። ስለሆነም ኤችአይቪ በደማቸው ውስጥ ለሚኖሩ እና በጣም ደካማ የበሽታ መቋቋም አቅም ላላቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።
የጎንዮሽ ጉዳቶች
ከክትባት በኋላ፡ አንዳንድ የጎንዮሽ ጉዳቶች ሊያጋጥምዎት ይችላል፡ ይህም በክትባቶች በጣም የተለመደ ነው። የጎንዮሽ ጉዳቶች ቁስል በክንድ ፡ ራስ ምታት እና ቀላል ትኩሳት ሊሆኑ ይችላሉ። ጥቂት ሰዎች ከባድ የአለርጂ ችግር ሊያጋጥማቸው ይችላል፡ ለዚህም ነው ክትባት ከተከተቡ በኋላ ለ 15-30 ደቂቃዎች በጤና እንክብካቤ ባለሙያ ቁጥጥር ስር መሆን ያለብዎት። ይህ በሁሉም ክትባቶች ላይ የሚተገበር ሲሆን፡ል ለኮቪድ-19 ክትባቶች የተለየ አይደለም። ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች፡ ከሌሎቹ አልፎ አልፎ ለሚከሰቱ ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ አይደለም።
ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች መከተብ አለባቸው?
ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች የኮቪድ-19 ክትባት በመውሰድ ከኤችአይቪ-ኔጋቲቭ ሰዎች ጋር ተመሳሳይ ጥቅም ይኖራቸዋል። ክትባቶቹ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ከባድ በሽታን ይከላከላሉ እና ተጨማሪ የቫይረሱ ስርጭትን ሊከላከሉ ይችላሉ። በመጨረሻው በተባለዉ ላይ አንዳንድ ጥርጣሬዎች አሉ ፣ እና ስለሆነም ሁሉም ሰው በደንብ ባወቅናቸው የመከላከያ እርምጃዎች እንዲቀጥል በጥብቅ ይመከራል፡ እጅዎን ይታጠቡ ፣ ርቀቶችዎን ይጠብቁ ፣ የአፍ መሸፈኛ ማስክ ያድርጉ እና ህመም ከተሰማዎት በቤት ውስጥ ይቆዩ ።
ዝቅተኛ የመከላከል አቅም እና ተጨማሪ በሽታዎች ያላቸው ሰዎች
የዛሬው የኤችአይቪ ሕክምና በኖርዌይ ውስጥ በሕክምና ላይ ያሉ አብዛኞቹ ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ጥሩ የበሽታ መቋቋም ሥርዓት አላቸው እና በደማቸው ውስጥ ያለው የቫይረስ መጠን ዝቅተኛ በመሆኑ በምርመራ ሊለካ አይችልም። በኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኡለቮል የሚገኘው የኢንፌክሽን በሽታዎች ክሊኒክ እንደገለጸው የበሽታ መከላከያ ስርአታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ማለትም የሲዲ 4 ቁጥር ከ350 በታች የሆኑ እና ሊለካ የሚችል የቫይረስ ቁጥር ያላቸው እና ተጨማሪ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብቻ ናቸው በኮቪድ-19 ለከባድ ህመም የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ሊሆን ይችላል።
በኤች አይ ቪ የተያዙ እና የተሳካ ህክምና ላይ ያሉ ሰዎች ለከባድ የኮቪድ-19 በሽታ የተጋለጡ አይደሉም።
ክትባቶች ኮሚርናትይ Comirnaty (ከፋይዝር Pfizer/ ባዮኤንቴክ BioNTech)፣ ሞዴርና Moderna እና ያንሰን Janssen ዝቅተኛ የመከላከያ ኣቅም ላላቸው ሰዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው። ያንሰን Janssen ክትባቱን የሚያዘጋጀው የጆንሰን እና ጆንሰን የፋርማሲዩቲካል ኩባንያ ነው።
የግል ሓኪሞች ግምገማ ያደርጋሉ
በኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ኡለቮል የሚገኘው ተላላፊ በሽታዎች የተመላላሽ ክሊኒክ፣ የኤችአይቪ ታማሚዎች ክትባቱ መሰጠት ያለበት ኮምዩነ እንጂ በተላላፊ በሽታዎች የተመላላሽ ታካሚ ክሊኒክ እንዳልሆነ አጽንኦት ይሰጣል። ለአደጋ የተጋለጡ ታካሚዎችን ለክትባት ሪፖርት የሚያደርጉት የግል ሓኪም ናቸው፣ ስለዚህ የግል ሓኪም የኤችአይቪ ህመሙ ማወቅ አስፈላጊ ነው። የግል ሓኪም በመደበኛነት የሲዲ 4 ደረጃ እና የቫይረሱ መጠን አስተያየት የተሰጠበትን የህክምና መዝገብ ማስታወሻ ቅጂ ይቀበላል። እነዚህ ማስታወሻዎች ታካሚው ለራሱ በhelsenorge.no ያገኛል።
Les også
schedule14.01.2023
→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?
ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።
schedule31.12.2021
→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።
በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።