ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

scheduleOppdatert: 06.03.2024

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ? (pdf)

መደበኛ ሃኪም(fastlege) ከአሎት በዚሁ መደበኛ ሃኪም አማካይነት ወደ አቅራቢዎ ወደ ሚገኘው የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና መስጫ ክፍል ወደ አለው ሃኪም ቤት እዲተላለፉ ያደርጋል። ነገር ግን መደበኛ ሀኪም ከሌሎት እርሶ በግልዎ በአቅራቢያዎ ወደ ሚገኘው ሆስፒታል የተላላፊ በሽታዎች ክፍል በመሄድ ተገቢውን ሕክምና ማግኘት ይችላሉ።

ኤች አይ ቪ ኖርዌይ ( HivNorge ) ከሚባለው ድርጅት ዕርዳታ ከፈለጉ እርዳታን መጠየቅ ይችላሉ። ይሔንንም ዕርዳታ የሚያገኙት ከዚህ ቀጥሎ በሚገኘው የኢሜይል አድራሻ ድብዳቤ በመጻፍ (post@hivnorge.no) ወይም በስልክ ቁጥር  +47 21 31 45 80 በመደወል ይሆናል።  ከሰኞ እስከ ዓርብ በአሉት የሥራ ቀናት ውስጥ በአውሮፓ አቆጣጠር ከጥዋቱ  09.00 ሰዓት እስከ 16.00 ሰዓት እኛን ማግኘት ይችላሉ። አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም አስተርጓሚ በማቅረብ እንታባበራን።

መደበኛ ሃኪም እንዴት ማግኘት ይቻላል?

በኖርዌ የሚኖር ማንኛውም ግለሰብ ሁሉ የሚታወቅበት ወይም ማንነቱ የሚገለጽበት መለያ ቁጥር ይሰጠዋል። ይህም የተወለደበትን ቀን፣ ወር፣ ዓመተምሕረት እና መንግሥት የሚሰጣቸው አምስት ቁጥሮችን ያካተተ መለያ ሲሆን ፣ ይህም የትውልድ ቀን እና የግል ቁጥር ያጣመረ ነው። አንዳንድ ግለሰቦች ደግሞ ዲ- ቁጥር ( d-nummer) የሚባል ሊኖራቸው ይችላል። እነዚህ ግለሰቦች ጊዜያዊ የሆነ መለያ ቁጥር የተሰጣቸው ሲሆን  ይህም የሚሆንበት ምክንያት ግለሰቦቹ የተለመደውን መለያ ቁጥር ለማግኘት ብቁ የሚያደርጋቸው አስፈላጊውን መስፍርቶች ማሟላት በማይችሉበት ወቅት ነው።

ማናቸውም በኖርዌ ውስጥ በሕዝብ መመዝገቢያ ውስጥ የተመዘገቡ እና በአንድ አውራጃ ውስጥ ኗሪ መሆናቸው ሲረጋገጥ መደበኛ ሃኪም የማግኘት መብት ስለሚኖራቸው መደበኛ ሃኪም ይደለድልላቸዋል። ዲ- ቁጥር (d-nummer) ያላቸው ግለሰቦች መደበኛ ሃኪም የማግኘት መብት የላቸውም። ነገር ግን ስደተኞች ከነቤተሰባቸው ይህ የማይመለከታቸው ሲሆን በሚኖሩበት አውራጃ መደበኛ ሃኪምን በሚመለከት ማንኛውንም በመጠየቅ ዕርዳት  ሊያገኙ ይችላሉ።  

መደበኛ ሃኪም የማግኘት መብትዎን በሚመለከት ጥርጣሬ ከአሎት ሔልሰ ኖርገ መመሪያ ( Veiledning helsenorge.no) በስልክ ቁጥር 23 32 70 00 በመደወል እርዳታ ማግኘት ይችላሉ።

ምን ዓይነት የኤች አይ ቪ ህክምናዎች ሊያገኙ ይችላሉ?

በኖርዌይ የኤች አይ ቪ ሕክምና ዓይነት የሚወሰነው በአነስተኛ ዋጋ እጅግ በጣም ውጤታማ የሆነ መደሀኒት ማቅረብ የሚችሉትን የመድሃኒት አቅራቢ ድርጅቶችን ከአወዳዳሩ በኋላ ብቃት ያለውን በመምረጥ ይወሰናል። ከዚያ በኋላ ምን ዓይነት የኤች አይ ቪ ህክምና ለመስጠት፣ ያሉት መድሀኒቶች እና ሕክምናዎች  በሙሉ እንደቅድሚያቸው በዝርዝር ይመዘገባሉ። በዝርዝሩ ውስጥ ያሉት ሁሉም መድሃኒቶች ጥሩዎች ናቸው። ነገር ግን ርስዎ በተለያዩ ምክንያቶች ዋጋቸው አነስተኛ የሆኑትን መድሃኒቶች ላይጠቀሙ ይችላሉ። ስለዚም ሌላ መድሀዲት የመጠቀም ዕድል ይሰጦታል ። እንደዚህ ዓይነት ምክንያቶች በሙሉ በጤና መዝገብዎ ላይ ይመዘገባል ።

ከዚህ በፊት ያልተጠቀሙት የኤች አይ ቪ ህክምና እንዲወስዱ ሊደረግም ይችላል ።

የሚከተሉትን ክትባቶችን እንዲከተቡ ይመከራል

በኖርዌይ ውስጥ የሚኖሩ የኤች አይ ቪ ሕሙማን የሚከተሉትን ክትባቶች እንዲከተቡ ይመከራል

  • የኮቪድ ክትባት እስከ ማጠናከሪያው (Covid-vaksine med booster-doser)
  • በየዓመቱ የኢንፍሉኤንይዛ ክትባትን እንዲከተቡ እንመክራለን
  • የኒዩሞኮክ ክትባትን ለሳንባ ምች ይረዳ ዘንድ እንዲከተቡ እንመክራለን(Pneumokokkvaksinering mot lungebetennelse. )
  • የሄፓቲት ኤ ወይም ቢ(hepatitt A og/eller B) መከተብ ያስፈልግዎት እንደሆነ ግምገማ ያስፈልጋል። ነገር ግን ከሌሎች ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግኑኘት ላላቸው ወንዶች  በሙሉ ሄፓቲት ቢ( hepatitt B) ክትባት በነጻ ይሰጣል።
  • 26 ዕድሜ በታች ላሉ በሙሉ እንዲሁም ከ40 ዓመት በታች የዕድሜ ክልል ውስጥ ከሚገኙ ወንዶች ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ያላቸው ወንዶች ኤ ፒ ቪ (HPV-vaksine) ክትባትባን እንዲከተቡ እንመክራለን።

እነዚህ ክትባቶችን በመደበኛ ሃኪምዎ አማካኝነት መከተብ ይችላሉ አለበለዚያ ደግሞ ከተቻለ በአካባቢዎ በሚገኘው ሃኪም ቤት በመሄድ የተላላፊ በሽታ ክፍል ውስጥ መከተብ ይችላሉ።

አንዳንዱቹ ክትባቶች ግለሰቡ ወይም በሽተኛው ሊከፍለው የሚገባው ክፍያ ሊኖረው ይችላል። ክትባቱን ከማዘዝዎ በፊት ክፍያ እንዳለው እና እንደሌለው መደበኛ ሃኪምዎን በመደወል በቅድሚያ ያጣሩ ።

ሙያዊ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ (Taushetsplikt)

ሙያዊ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታ (Taushetsplikt) ግላዊ የሆኑ መግለጫዎች እና የጤና ነክ መግለጫዎች ወደ የማይመለከታቸው ግለሰቦች እንዳይደርስ ጥበቃ ሊሰጥ የሚችል ወይም የሚከላከል ግዴታ ነው ።

ማንኛውም በጤና ተቋም ውስጥ ፣ በሃኪም ቤቶች ወይም በሃኪም ቢሮዎች እና በመሳስሉት አገልግሎት የሚሰጡ ግለሰቦች በሙሉ ሙያዊ ምስጢር የመጠበቅ በሕግ የተደነገገ ግዴታ አለባቸው። የጤና ተቋማት ሠራተኞች ወይም አገልጋዮች በሙሉ ይህ ሙያዊ ምስጢር የመጠበቅ ግዴት የተደነገገው የጤና ተቋም አገልጋዮች ሕግ (helsepersonelloven) ሲሆን፣ ማን የጤና ተቋም አገልጋይ እንደሆነ ደግሞ በጤና ተቋም ሕግ አንቀጽ  3 (helsepersonellovens § 3) በተገለጸው መሠረት ይሆናል ።

ሌሎች ግለሰቦች ከሐኪሞች ማዕከል ጋር ግንኙነት ያላቸው በሙሉ ፣ እንደ የጽዳት ሠራተኞች፣ የሕንጻ ጥገና እና ጥበቃ አገልጋዮች እንዲሁም የቢሮ ሠራተኞች በሙሉ ሙያዊ ምስጢር የመጠበቅ ግዴታቸው የተደነገገው በአስተዳደር ሕግ አንቀጽ  13 (forvaltningslovens § 13) መሠረት ነው።

ከኤች አይ ቪ ጋር ስለ መኖር የሚመለከት ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ ከአሎት ሒቭ ኖርገን( HivNorge) በማግኘት መጠየቅ ይችላሉ።

Les også

schedule14.01.2023

→ ለኖርዌይ እንግዳ ከሆኑ የኤች አይ ቪ መድህኒት ይፈልጋሉ?

ማናቸውም የኤች አይ ቪ ሁሙማን የሆኑ እና በኖርዌ አገር ውስጥ የሚኖሩ ሁሉ ነጻ ሕክምና የማግኘት መብት አላቸው። ሕሙማኑ ተገቢውን ሕክምና የሚያገኙት በአቅራቢያቸው በሚገኘው ሃኪም ቤት የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና በሚሰጥበት ክፍል ይሆናል።

schedule31.12.2021

→ ደህንነቱ የተጠበቀ የኮቪድ-19 ክትባት።

በኮቪድ-19 ላይ የሚወሰዱ ክትባቶች ኤችአይቪ ላለባቸው ሰዎች ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ዩኤንኤድስ UNAIDS አስታወቀ። በኖርዌይ የሚገኝ የተላላፊ በሽታዎች ዶክተሮች ይህንን ይደግፋሉ እና ከኤችአይቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ክትባቱን እንዲወስዱ ያበረታታሉ።