camera_altCrestock
ኮሮናቫይረስእናኤችአይቪ
በሆስፒታሎች ውስጥ ለኤች.አይ.ቪ እና ለኮሮና ቫይረስ ህክምና የሚሰጠው ክፍል አንድ ከመሆኑ የተነሳ የአብዛኞቹ ሆስፒታሎች የዚህ ህክምና ሰጪ ክፍሎች በስራ ተወጥረዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ኤች አይ ቪ ያላቸው ሰዎች በሙሉ ለአስፈላጊ ክትትል ፣ የመድኃኒት ማዘዣ ለማሳደስ እና ለመሳሰሉት አገልግሎቶች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸው እርግጠኛ መሆን ይችላሉ ፡፡
በኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒኩ ለኤች አይ ቪ ታካሚዎች ክትትል ለማድረግ የሚውል የራሱን የአሰራር ደንብ አውጥቷል ፡፡ ኤች አይ ቪ ኖርዌይ (HivNorge) ከክሊኒኩ ጋር በየጊዜው ይገናኛል እንዲሁም ስለ ወቅታዊ የአሰራር ደንብ መረጃ በድረ ገጾቹ. ያወጣል።
በቅርቡኤችአይቪእንዳለባቸውተነግሯቸውከኡለቮልሆስፒታልውጤቶችንእየተጠባ በቁያሉሰዎችየምርመራውጤቶቹእንደደረሱወዲያዉኑየተለመደውክትትልይደረግላቸዋል፡፡
ኤች አይ ቪ ኖሯቸው የሚወስዱት መድሀኒቱ በደንብ የሰራላቸው እና ከባድ ከሆኑ ተጨማሪ በሽታዎች ነጻ የሆኑ አብዛኞቹ ኮቪድ-19 ቫይረስ ቢተላለፍባቸው እንደ ማንኛውም ጠንካራ የሆነ በሽታ የመከላከል አቅም አላቸው።
ኤች አይ ቪ ተሸካሚዎች መካከል ጥቂቶቹ ዘላቂ የሆነ ዝቅተኛ የCD-4 ህዋሳቶች ቁጥር እና፣ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ለመተንፈሻ አካላት ልክፈቶች ትንሽ በበለጠ የሚያጋልጥ ዝቅተኛ የሆነ በሽታን የመከላከል ስርዓት ሊኖራቸው ይችላል። አንድ ሰው ኤች አይ ቪ ስላለው በኮሮና ቫይረስ የመያዝ አደጋ አላቸው ከሚባሉት ውስጥ ሊያካትተው ይችላል ወይ ወይም በቫይረሱ ቢያዝ በከባድ ደረጃ ሊታመም ይችላል ወይ የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ለኤች አ ይቪ ኖርዌይ (HivNorge) ይቀርባሉ። የኡለቮል ሆስፒታል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ሃላፊ የሚከተሉትን መልሶች ሰጥተውናል:
እ.ኤ.አ. እስከ 17.03.2020 ድረስባለንመረጃኤች.አይ.ቪየኮቪድ -19ንቫይረስወደከባድየበሽታደረጃየማድረስአደጋአለውየሚልድምዳሜላይአልተደረሰም፡፡
የኖርዌይየጤናዳይሬክቶሬቱማርች 23 ላይባወጣውየተሻሻለመረጃደካማየሆነበሽታየመከላከልአቅምያላቸውሰዎችንለኮሮናበሽታበተለየመልኩከተጋለጡቡድኖች መካከልአካቷቸዋል፡፡ይህየዘለቀየCD-4 ህዋሳቶችቁጥርማነስያላቸውየኤችአይቪተሸካሚዎችመካከልአብዛኞቹንያካትታል።
ሌሎቹ የሚያሰጋቸው ቡድኖች የዕድሜ መግፋት፣ ውስጥ ለውስጥ ስር የሰደዱ እንደ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ ፣ ስር ሰደድ የሳንባ በሽታ ፣ ካንሰር ፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው እና ሲጋራ አጫሾች ሲሆኑ እነዚህ በኮሮና ቫይረስ ቢያዙ በከባድ የመታመም እድላቸው ከፍተኛ ነው።
የCD-4 ህዋሳቶቾ ቁጥር ዝቅተኛ ከሆነ እና ሌሎች ከባድ ህመሞች ካለቦት የመንግስት መስርያ ቤቶችን ምክሮች በደንብ መከተል በጣም አስፈላጊ ነው. እርጋታ በሚያገኙበት በቤቶ ውስጥ እራሶን ቢያገሉ እና ላላስፈላጊ ነገሮች ከቤት ባይወጡ ፣ ከሌሎች ጋር ባይሰባሰቡ እና እንዲሁም ባይገናኙ የተሻለ ነው።
አሁንም ገና በእርግጠኝነት ያልታወቁ ብዙ ነገሮች አሉ፡፡ የኖርዌይ የሕዝብ ጤና ተቋም (ኤፍ.ሆ.ኢ) የራሱ የሆነ ስለ በሽታው በተለየ መልኩ ስለሚያሰጋቸው ሰዎች ወቅታዊ መረጃዎችን በተከታታይ የሚያወጣበት ድረገጽአለው።
አይ.ኤ.ኤስ. (ዓለም አቀፍ ኤድስ ማህበር) አርብ ኤፕሪል 3 ቀን በኢንተርኔት ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ከቀረቡት መካከል የአለም አቀፉ የጤና ተቋም ከኤች.አይ.ቪ እና ከኮሮና በሽታ ጋር በተያያዘ ያካበታቸውን ተሞክሮዎች አንዱ ነበር።
እስከ አሁን ባለው መረጃ በኮቪድ 19 የታመሙ የኤች አይ ቪ ተሸካሚዎች (በዓለም ዙሪያ) በአንጻራዊነት ጥቂቶች ናቸው። ስለዚህ ኤች አይ ቪ እና ኮቪድ -19 አያይዞ የተሰራ ጥናት የለም፥ ነገር ግን የተካበቱ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት:
- የCD-4 ህዋሳቶች ቁጥር ይብዛም ይነስም፥ የኤች.አይ.ቪ ተሸካሚ መሆን ብቻ በኮቪድ 19 የመሞት ወይም በጠና የመታመም አደጋ ላይ አይጥልም።
- በሽታ የመከላከል አቅም ደካማ መሆን በቫይረሱ የመያዝ አደጋን ከፍ ያደርጋል እንጂ በጠና የመታመምን ወይም የመሞት አደጋን አይጨምርም። የCD-4 ህዋሳቶቻቸው ቁጥር ከ 200 በታች የሆነ ሰዎች በቫይረሱ ላለመለከፍ የሚረዳ ለየት ያለ የጥንቃቄ እርምጃ እንዲወስዱ ይመከራሉ።
- ምንምእንኳየኤች.አይ.ቪተሸካሚመሆንብቻበኮቪድ 19 በጠናየመታመምአደጋላይአይጥልም፥ኤችአይቪ ለረጅምጊዜተሸክመውየኖሩለበሽታየመጋለጥአደጋቸውንከፍየሚያደርጉምክንያቶችያሏቸውአንዳንድሰዎችአሉ፡፡ይህአደጋበተለይኤድስየነበረባቸውእናከኤድስጋርተያያዥነትያለውየሳንባምችወይምሌላየሳንባበሽታላላቸውሰዎችይመለከታል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት ተሞክሮ ከኖርዌይ የጤና ባለሥልጣናት ከሚሰጡት ምክሮች ጋር ይመሳሰላል፡፡ ጉባኤውን ሙሉ በሙሉ እዚህ ማየት ይችላሉ ፡፡ ጉባኤው የሚካሄደው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው፡፡
በበሽታ የመያዝ እድል ጋር በተያያዘ ስለ ኤች.አይ.ቪ ሁኔታዎ ለአሰሪዎም ይሁን ለሌሎች ሰዎች ከራስዎ ፍላጎት ውጭ መንገር አያስፈልጎትም።
የኖርዌይ የህዝብ ጤና ተቋም ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አጠቃላይ ምክር እና በኖርዌይ ስላለው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃን በተመለከተ እዚህ ላይ ማንበብ ይችላሉ ፡፡
ትኩሳት እና የመተንፈሻ አካላት ህመም ከያዞት ምናልባት ቫይረሱ ተላልፎቦት ከሆነ ለማጣራት ሐኪምዎን በማነጋገር ምርመራ እንዲደረግሎት ይጠይቁ ፡፡ ሐኪሞ የተላላፊ በሽታ ቅድመ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ፥ አስቀድመው ቀጠሮ ሳያስይዙ እና ሳይፈቀድሎት ወደ ሐኪም ቤት በአካል መሄድ የለቦትም፡፡ ምሽት እና ቅዳሜና እሁድ የድንገተኛ ህክምና ክፍልን ማነጋገር ይችላሉ ፡፡
የኤችአይቪመድሃኒቶችንለኮርናቫይረስመጠቀም
በአሁኑ ጊዜ ኮቪ ድ-19ን በኤችአይቪ መድሃኒቶች ለማከም ሙከራዎች እየተደረጉ ናቸው ፡፡ ሙከራዎቹ የሚካሄዱት በአሁኑ ወቅት ለኤች አይ ቪ ህክምና ብዙም የማይታዘዙ መድኃኒቶች ላይ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ ኤችአይቪ ያላቸው ሰዎች የሚወስዷቸው መድኃኒት አቅርቦት ላይ ይህ ምንም ተጽእኖ እንደማይፈጥር የጤና ባለሥልጣኖቹ ያረጋግጣሉ፡፡
እንዲሁም ኤች አይ ቪ ህክምና መውሰድ በራሱ በኮቪድ -19 ቫይረስ ያስይዛል ወይም የቫረሱ አስተላላፊ ያደርጋል የሚል ምንም አይነት መረጃ የለም ፡፡
የኑመካከስክትባት
ኑመኮክ በሚሰኝ ባክቴርያ የሚመጣን የሳምባ ምች ለመከላከል የሚረዳው የኑመካከስ ክትባት ትኩረት አግኝቷል፡፡ ከኮሮና ቫይረስ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም ፣ ነገር ግን ለቫይረሱ ተጋላጭነት ያላቸው ሰዎች ይህን ቢወስዱ የጤና ማእከላቶች እንዳይጨናነቁ ይረዳል፡፡
ኤች አይ ቪ ያለባቸው ሰዎች በሙሉ ከተላላፊ በሽታ ህክምና ጋር በተያያዘ የመጀመሪያዎቹ ምርመራዎቻቸው ላይ የኑመካከስ ክትባት የመውሰድ እድል ይሰጣቸዋል፡፡ ስለዚህ አባዛኞቹ ክትባቱን የመውሰድ እድል ተሰጥቷቸዋል። አሁን የክትባት እጥረት ስላለ፥ መውሰድ የሚችሉት ከዚህ በፊት እድሉ ላልተሰጣቸው እና በእንደዚህ ዓይነት የሳንባ ምች ምክንያት በጠና የመታመም እድላቸው በጣም የባሰ ለሆኑት ብቻ ነው ፡፡
የኡለቮል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒክ ክፍሉ እድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ ለሆኑ ከዚህ በፊት ክትባቱን ላልወሰዱ ታካሚዎቻቸው በሙሉ ይህን ክትባት የመውሰድ እድል እየሰጠ ነው፡፡
Les også
schedule19.12.2024
→ Innovasjoner i kampen mot hiv i krigsherjede Ukraina
I et land hvor krig og stadige militære angrep er en alvorlig belastning også for helsesystemet, opprettholder Ukraina tilgangen på hivmedisiner og forebyggende hivbehandling, og utvikler også nye metoder for å ivareta landets innbyggere som lever med hiv.
schedule18.12.2024
→ HivNorge søker ny kollega
Motiveres du av arbeid for rettigheter, likeverd og mangfold? Og mot diskriminering og stigma? HivNorge søker en rådgiver i 100% stilling, i en dynamisk og innflytelsesrik organisasjon.