ስለ ኦስሎ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒክ ወቅታዊ መረጃ

የኡለቮል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒኩ ከአርብ 13 ማርች ጀምሮ አገልግሎት የሚሰጠው ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ነው፡፡ የተመላላሽ ክሊኒክ ሕንፃዎች ለመጪዎቹ ሳምንታት የሚዘጉ ሲሆን ፣ የዲጂታል የተመላላሽ ክሊኒኩ ግን ሙሉ በሙሉ ይሠራል፡፡ አሰራሩ እንደሚከተለው ነው:

scheduleOppdatert: 16.04.2020

createForfatter: Sekretariatet

labelEmner:

ለምርመራ ወደ ተመላላሽ ክሊኒኩ መቅረብ የነበረባቸው የኤች አይ ቪ  ታካሚዎች የደም ናሙና መስጠት እና የምርመራ ቀጠሯቸው ስለመሰረዙ መልእክት ይደርሳቸዋል። ያም ሆኖ ግን የቀጠሮ ቀኑ በሐኪሙ የቀጠሮ መጽሐፍ ውስጥ እንደሰፈረ ይቆያል ፡፡ ሐኪሙየታካሚውን ሰነድ ያነባል ፣ የበፊት የደም ናሙና  ምርመራዎችን ያያል፣ የመጨረሻው የህክምና ቀጠሮ ላይ የተጻፈውን ማስታወሻዎች ያነባል፣ ኤሌክትሮኒካዊ የመድሃኒት ማዛዣ ይልካል፣  ማስታወሻዎሻ ይጽፋል እንዲሁም ለአዲስ የህክምና ክትትል በቀጠሮ ይጠራል። ሐኪሙ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ለታካሚው ይደውላል። የህክምና ሰነዶን  www.helsenorge.no  ውስጥ ገብተው “pasientjournal” የሚለውን ከተጫኑ በኋላ የክልሎ የጤና ቢሮ የሆነውን Helse Sør-Øst for Oslo Universitetssykehus የሚለውን በመምረጥ ከፍተው ማንበብ ይችላሉ፥ ወይም ደግሞ  minjournal.no  ውስጥ ገብተው «journaldokumenter» ተጭነው በመክፈት ማየት ይችላሉ። 

በቅርቡኤችአይቪእንዳለባቸውተነግሯቸውከኡለቮልሆስፒታልውጤቶችንእየተጠባ በቁያሉሰዎችየምርመራውጤቶቹእንደደረሱወዲያዉኑየተለመደውክትትልይደረግላቸዋል፡፡ 

minjournal / helsenorge.no ውስጥ በሚከተለው መልኩ ከፍተው መግባት ይችላሉ:

በተመላላሽ ክሊኒኩ ውስጥ በየቀኑ ፀሐፊ ፣ ነርስ እና ሐኪም ይኖራሉ፡፡ አንዳንድ ታካሚዎችም በልዩ ቀጠሮ መምጣት ይችላሉ፡፡ እነዚህ ታካሚዎች በእግር በብስክሌት ወይም በግል መኪናቸው ቢመጡ በጣም ይመረጣል። ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ በሽተኞች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ሰው እንዲረዳው በተመላላሽ ክሊኒኩ ውስጥ የክፍል ኃላፊና ልዩ ሐኪም ቤንተ ማግኒ ይጠይቃሉ፡፡ የተመላላሽ ክሊኒኩ የኤች አይ ቪ ታካሚዎች  በሙሉ ማለት ይቻላል በጥሩ ሁኔታ በሽታውን መቆጣጠር ስለሚችሉ የደም ናሙና  ምርመራዎቹ ትንሽ መዘግየት የሚያሳሳብ ነገር አይደለም፡፡ 

ለኤችአይመድኃኒቶችአዲስየመድኃኒትማዘዣንበተመለከተ

በየቀኑ ከሚወስዱት የኤች አይ ቪ መድሃኒትዎ ምን ያህል እንደቀሮት ይዩ። ሁለት ወይም ሶስት ወራት የሚያዘልቅ መድሃኒት ካሎት  አዲስ የታዘዘን መድሀኒት የግድ በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ውስጥ ሂደው ማውጣት አያስፈልጎትም፡፡ Apotek1 i Storgata  የመድኃኒት ቤት ማንኛውንም የኤችአይቪ መድኃኒቶች ማግኘት እና በአጭር ጊዜ ውስጥ የበለጠ ማዘዝ ይችላል። 

በቅርቡ ወይም ደግሞ በመጭዎቹ አጭር ጊዜያቶች ውስጥ የሃኪም ቀጠሮ ካሎት፥ የመድኃኒት ማዘዣው ለቀጠሮ ሊቀርቡ ታስቦ በነበረው እለት ወዲያውኑ ይታደሳል፡፡ የመድኃኒት ማዘዣው ላይ ስህተት ካለ ወይም ለቀጠሮ ሊቀርቡ ታስቦ ከነበረው እለት በፊት መድሃኒት ካስፈለጎት፥ ለኤች አይ ቪ ኖርዌይ (HivNorge) ይንገሩ እኛም መልእክቶን ለተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒኩ እናደርሳለን፡፡

ሐኪምዎ የመድኃኒት ማዘዣውን ካደሰሎት  www.helsenorge.no ከፍተው በመግባት «pasientjournal» የሚለውን ከተጫኑ በኋላ የክልሎ የጤና ቢሮ የሆነውን Helse Sør-Øst for Oslo Universitetssykehus የሚለውን በመምረጥ ስለ ማዘዣው ማንበብ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም  «Legemidler» የሚለውን በመጫን የመድኃኒት ማዘዣውን ማግኘት ይችላሉ ፡፡ 

ኦስሎ ከሚገኘው ከ Apotek1 i Storgaten  የመድኃኒት ቤት ጋር በመተባበር የመድኃኒት ማዘዣውን በዲጂታላዊ መልኩ ማግኘት ለሚቸግራቸው ሰዎች የሚረዳ መፍትሔም ተበጅቷል። የ Apotek1 i Storgata  መድኃኒት ቤት መደበኛ ደንበኛ ካልሆኑ እና ከተቸገሩ የመድሃኒቶቹ ተጠቃሚ እንደሆኑ የሚያሳይ የመድኃኒት/ቶች ማኖርያ ሳጥን ወደ መድኃኒት ቤቱ ወስደው በማሳየት መድሃኒቶቹን ማግኘት ይችላሉ ፡፡ እንዲሁም የኡለቮል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና የተመላላሽ ክሊኒክ ታካሚ ሆነው ሳለ ነገር ግን መኖርያዎ ከኦሎሎ ውጭ ከሆነ እና ወደ ከተማ መምጣት ካልቻሉ መድኃኒት ቤቱን በስልክ በመደወል መድኃኒቶችን ማዘዝ ይችላሉ ፡፡ (ማንነቶን የሚያሳይ) መታወቂያ  መያዝን አይርሱ፡፡

ቤት መቆየትን ከመረጡ ወይም መገለል ካለቦት መድኃኒት ቤቱ መድኃኒቱን በፖስታ ሊልክሎት ይችላል። ይህን በተመለከተ ለበለጠ መረጃ መድኃኒት ቤቱ በቀጥታ ያነጋግሩ ፡፡

እንዲሁም ይህ እንዴት እንደሚካሄድ መረዳት ከተሳኖ ኤች አይ ቪ ኖርዌይ (HivNorge) እንዲረዳዎ መጠየቅ ይችላሉ። ኤች አይ ቪ ኖርዌይ (HivNorge) በኢሜይል  post@hivnorge.no ወይም በስልክ ቁጥር 21 31 45 80 ወይም 920 16 892 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

የመድኃኒትማዘዣለሚያስፈልጋቸውየውጭአገርዜጎች 

የኖርዌይ ሆስፒታል ታካሚ ያልሆኑ ግን ኦስሎን ለቀው መውጣት ያልቻሉ የኤችአይቪ መድሃኒት የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ወደ ኤች አይ ቪ ኖርዌይ (HivNorge) በስልክ 920 16 892 ከደውሉ መልእክታቸውን ለተላላፊ በሽታ የተመላላሽ ክሊኒክ እንዳርሳለን፡፡ ለኤች አይ ቪ ህክምናዎ የሚረዳ የመድኃኒት ማዘዣ እንዲያገኙ ክሊኒኩ ይተባበርዎታል፡፡

ኮሮናእናኤችአይ

አንድ ሰው ኤች አይ ቪ ስላለው በኮሮና ቫይረስ የመያዝ አደጋ አላቸው ከሚባሉት ውስጥ ሊያካትተው ይችላል ወይ ወይም በቫይረሱ ቢያዝ በከባድ ደረጃ ሊታመም ይችላል ወይ የሚሉ  በርካታ ጥያቄዎች ለኤች አ ይቪ  ኖርዌይ (HivNorge) ይቀርባሉ። የኡለቮል ሆስፒታል የተላላፊ በሽታዎች ሕክምና ክፍል ሃላፊ የሚከተሉትን መልሶች ሰጥተውናል:

... እስከ 17.03.2020 ድረስባለንመረጃኤች.አይ.የኮቪድ -19ቫይረስወደከባድየበሽታደረጃየማድረስአደጋአለውየሚልድምዳሜላይአልተደረሰም፡፡ 

የኖርዌይየጤናዳይሬክቶሬቱማርች 23 ላይባወጣውየተሻሻለመረጃደካማየሆነበሽታየመከላከልአቅምያላቸውሰዎችንለኮሮናበሽታበተለየመልኩከተጋለጡቡድኖች  መካከልአካቷቸዋል፡፡ይህየዘለቀCD-4 ህዋሳቶችቁጥርማነስያላቸውየኤችአይተሸካሚዎችመካከልአብዛኞቹንያካትታል። 

ሌሎቹ  የሚያሰጋቸው ቡድኖች   የዕድሜ መግፋት፣ ውስጥ ለውስጥ ስር የሰደዱ እንደ የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ ፣ ስር ሰደድ የሳንባ በሽታ ፣ ካንሰር ፣  ከፍተኛ የደም ግፊት ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ያለባቸው እና ሲጋራ አጫሾች ሲሆኑ እነዚህ በኮሮና ቫይረስ ቢያዙ በከባድ የመታመም እድላቸው ከፍተኛ ነው። 

የCD-4 ህዋሳቶች ቁጥር ማነስ እና ሌሎች ከባድ ህመሞች ካለቦት  የመንግስት መስርያ ቤቶችን ምክሮች በደንብ መከተል በጣም አስፈላጊ ነው.

ከኖርዌይ የህዝብ ጤና ተቋም ለጥያቄዎ የሚሆን መልስ ማግኘት ካልቻሉ ኤች አ ይቪ  ኖርዌይ (HivNorge)ን መጠየቅ ይችላሉ። ኤች አ ይቪ  ኖርዌይ (HivNorge) ከኡለቮል የተላላፊ በሽታ የተመላላሽ ክሊኒክ ጋር የቅርብ ግንኙነት ስላለው፣ ምናልባትም ህክምና ነክ የሆኑ ጥያቄዎች ካሎት የተላላፊ በሽታ ሃኪሞችን አነጋግረን መልሱን በተቻለን ፍጥነት እንሰጥዎታለን ፡፡

የኖርዌይ የህዝብ ጤና ተቋም ለህብረተሰቡ የሚሰጠው አጠቃላይ ምክር እና በኖርዌይ ስላለው ሁኔታ ወቅታዊ መረጃን በተመለከተ እዚህ ላይ ማንበብ ይችላሉ ፡፡

Les også

schedule27.09.2023

→ PrEP på agendaen

Som en del Fast Track Cities 2023-konferansen i Amsterdam har HivNorge deltatt på flere foredrag og erfaringsutvekslinger om den hiv-forebyggende behandlingen PrEP. PrEP er et viktig og aktuelt tema under konferansen, siden introduksjonen av PrEP har bidratt til stor reduksjon av nye hivtilfeller globalt.

schedule26.09.2023

→ Fast Track Cities 2023-konferansen er i gang

Fagpersoner, aktivister og berørte på hivfeltet er samlet for å dele erfaringer, presentere forskningsresultater og for å styrke det internasjonale nettverket. – Arbeidet for å ende hivepidemien er ikke bare medisinsk, i dag er den største utfordringen stigmaet og de sosiale belastningene relatert til hiv, forteller Amsterdams ordfører.